በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ቄራ ጐፋ የገበያ ማዕከል ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 19 መደብሮች ሙሉ በሙሉ ወደሙ፡፡ ጥር 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሌሊቱ 7፡15 ሰዓት ላይ የእሳት ቃጠሎው እንደተከሰተ የገለጹት፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ ናቸው፡፡ የእሳቱ መነሻ ምክንያትና በንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን [...]
↧