ኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ከጀመሩ ዘንድሮ 111ኛ ዓመታቸውን ይዘዋል። በቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ምንሊክና በአሜሪካው አቻቸው ፕሬዚዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት ልዑካን መካከል ለዘጠኝ ቀናት ድርድር ከተካሄደ በሁዋላ ነበር ግንኙነቱ በይፋ የተጀመረው። ከአንድ ክፍለ-ዘመን በላይ ያስቆጠረው የአገራቱን ግንኙነት በመጠቀም ኢትዮጵያ ጠቀም ያለ እርዳታዎችን ተቀብላለች።በአሁኑ ወቅትም በየዓመቱ ከ500 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የልማትና የወታደራዊ እርዳታ ተጠቃሚ ናት። አሜሪካም [...]
↧