ኩርዳዊ ነኝ ከኢራን – ኢማን አባስ እባላለሁ በቋንቋዬ እንዳልቀኝ – እንዳልከትብም ሁኛለሁ፤ የኔ ጌቶች ያሻቸውን – እሆን ዘንዳ ቢያስጨንቁኝ ግዳይ ጣልኩኝ እራሴን – ጭካኔያቸው ቢብሰኝ፤ ያውላችሁ ያሻችሁት – እንዳልሆን እሆን ፍርዳቸሁ አንደበቴን ተቆልፌ – ዐይኖቼን ተለጉሜ ይመቻችሁ እላለሁ – ጆሮቼን አስከርችሜ፤ ብእሬን ወርውሬ – ቀለሙን ደፍቼ ፍረዱኝ እላለሁ – እናንት ወገኖቼ፤ (ለምሥራቅ ኩርድ ባለቅኔው [...]
↧