“የአካኪ ዘራፍ ፖለቲካና ከስሜት ያልጸዳ የፖለቲካ ትግል መሪውንም ሆነ አምኖ የሚመራውን ህዝብ ለድል” እንደማያበቃ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ። ከኤርትራ ጋር ስምምነት ቢደረግ መልካም መሆኑን፣ ነገር ግን ስምምነቱ የመሪዎችና የፖለቲከኞች ሳይሆን የህዝብን ስሜት የጠበቀ ሊሆን እንደሚገባውም ጠቁመዋል። ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጋር በተለይ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፕ/ር በየነ “አሁን ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስተዋይነት [...]
↧