“አስካውት!…” “ምን ጊዜም ዝግጁ!!!” ዱሮ ዱሮና በኛም ዘመን የቦይ እስካውት ክለብ (Boy Scout) እንቅስቃሴ ሞቅና ደመቅ ያለ ነበር፡፡ ሰላሌ ፍቼ፣ የአበራና አስፋው ወሰን የ1ኛ ደረጃና ወሊሶ የደጃዘማች ገረሱ ዱኪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ እያለሁ (ከ1953-1960 ዓ.ም.) የቦይ እስካውት ክለብ አባል ነበርኩ፡፡ ፍቼ እያለን፣ የእስካውት ክለባችን ኃላፊ መምህር ወልዴ ይባሉ ነበር፡፡ በእግራችን ወደ ገጠር እየተጓዝን [...]
↧