የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አራት ኪሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ጆሊ ባር፣ ኮጆሊ ባር ወደ አራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ለመሸጋገርያ የሚያገለግል የብረት መሰላል መሥራቱ ይታወሳል፡፡ ባለሥልጣኑ ይህንን መሸጋገሪያ መሰላል የሠራው፣ በአካባቢው የሚተላለፈው የሕዝብ ብዛት ከሌሎች አካባቢዎች የበዛ ስለሆነ፣ የትራፊክ መጨናነቅና በየቀኑ በተሽከርካሪ አደጋ እየተቀጠፈ ያለውን የሰው ሕይወት (ምንም በተባሉት ቦታዎች እስካሁን የከፋ አደጋ ባይደርስም) ለመታደግ በሚል መሆኑ [...]
↧