ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ በዓሎቻቸውን ስለየበዓላቱ ትርጉም ባላቸው ዝማሬዎችና ጭፈራዎች ያደምቁታል፡፡ ከእነዚህ አንዱ የሆነው የዘመን መለወጫንም ‹‹እንቁጣጣሽ››ን በ‹‹አበባ አየሽ ሆይ›› ያደምቁታል፡፡ እንቁጣጣሽ ሲመጣ ልጃገረዶች ከበሯቸውን ይዘው በየቤቱ እየዞሩ ‹‹አበባ አየሽ ሆይ›› እያሉ ሲጨፍሩ፣ ድምፃዊቷ ዘሪቱ ጌታነህም በየራዲዮ ጣቢያው ‹‹እንቁጣጣሽ እንኳን መጣሽ…›› እያለች በቀጭኑ ድምጿ የምታቀነቅነው ዘፈን ሲሰማ በዓሉን ለመቀበል ያለውን ስሜት ሞቅ ሞቅ ያደርጋል፡፡ ቀደም ሲል [...]
↧