በኢትዮጵያ የአጼዎች እና የሥልጣኔ መናገሻነት ስማቸው ከሚጠቁሱት ታሪካዊ ስፍራዎች መካከል ጎንደር አንዷ ናት። ጎንደርን ማዕከል ያደረገው የ17ኛው እና የ18ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ የእድገት፣ የምርት መፍለቂያ፣ የሃይማኖት ማዕከል እንዲሁም በኪነጥበብ ታላቅ ስፍራ የደረሰችበት ወቅት እንደሆነ ይጠቀሳል።። የእነዚህ ታላላቅ ተግባራት ማሳያዎች መካከል ደግሞ ከጎንደር ነገሥታት መካከል አንዱ በነበሩት አጼ ፋሲለደስ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተገነባው የፋሲል ግንብ ነው። […]
↧