አባዬ – አለው የገበሬው ልጅአቤት – አለ አባቱ።ይሄ የምሰማው ድምጽ ምንድን ነው?የጃርቶች ድምጽ ነው ልጄ።ባለፈው ስታርስ ጮኹ። ስትዘራ ጮኹ። ስታጭድ ጮኹ- አለው ልጁ።ልክ ነህ – መለሰለት አባቱ።ለምን?- አለ ልጅ።የጃርት ጠባዩ ነው። ጃርት ይጮኻል እንጂ አይሠራም። ጃርት አያርስም፤ ስታርስ ይጮሃል። ጃርት አይዘራም፤ ስትዘራ ይጮሃል። አያጭድም፤ ስታጭድ ይጮሃል – አለው አባቱ።ለምን? – ደግሞ ጠየቀ ልጁ።ጃርት ከጮኸ እየሠራህ […]
↧