ክፍለ ጦሩ በሸኔ ላይ እየተወሠደ ያለውን ወታደራዊ እርምጃ ለማጠናከር በጉጂ ዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ሚሊሻዎችን በማሰልጠን የቀጠናውን ሠላምና ፀጥታ በማረጋገጡ ረገድ ውጤታማ ሥራ መሠራቱን አሥታውቋል፡፡ የስልጠናው ዋና አስተባባሪ ሻምበል ባቡ ባላባት እንደገለፁት የፀረ ሽምቅ ግዳጅን በብቃት ከመወጣት ጎን ለጎን የዞኑን የፀጥታ ሀይል ለማጠናከር በርካታ ሚሊሻዎችን የአካል ብቃት የስልት እንዲሁም የተኩስ ልምምድ ሥልጠና በመስጠት ማሥመረቅ ተችሏል፡፡ […]
↧