“ለዐማራነቴ፤ ለኢትዮጵያዊያነቴ ህይወቴን እሰጣለሁ” እንዳልህ ይኼው ደማህ፤ ልክ እንደ አድዋው ጀግና ፊታውራሪ ገበየሁ “ህወሓትን ፈርቼ ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ፤ ከፊት ለፊት ስፋለም ከወደቅሁ ግን ልጆቼን አደራ” እንዳልህ ክንድህ ላይ በፈሰሰው የደም ጠብታ ቃልኪዳንህን አፀናህ። ባለፈ ጊዜ ለእረፍት መጥቶ ሚስቱ “እባክህ በልጆችህ ልለምንህ አትሂድ” ስትለው “ልጆቼ ከሀገሬ አይበልጡም” ነበር ያላት። በርግጥ ይህ የአባቶቻችን ውርስ ነው። […]
↧