ጀግንነቱን ዓለም መስክሮለታል፣ ስሙን ከፍ አድርጎ ጠርቶታል፣ ታሪክ በማይጠፋ ቀለም፣ በማያረጅ ብራና አስፍሮታል፡፡ ጠላት ሮጦለታል፣ በስሙ ተሸብሮለታል፣ ከእግሩ ሥር ወድቆ ይማሩኝ ንጉሥ ኾይ ብሎለታል፡፡ በጀግንነቱ በጠላቶቹ ልብ ላይ የነገሠ፣ በዝናው ዓለምን ያዳረሰ፣ የጠላቶቹን አንጀት የበጠሰ፣ የወዳጆቹን አንጀት ያራሰ ጀግና ነው እርሱ፡፡ የማይገመት ልብ ያለው፣ ጠላት የማይችለው፣ ጀግንነት፣ ብልሃት፣ አሸናፊነትና ጽናት የታደለው ኃያል ንጉሥ፡፡ ነጭ ባየለበት […]
↧