የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737-800 ማክስ አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ በደረሰበት ስፍራ ለሚገነባው ሀውልትና ፓርክ የወጣውን ዓለም አቀፍ የንድፍ ውድድር የኢትዮጵያዊው አርክቴክት አለበል ደስታ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ታውቋል። በምስራቅ ሸዋ ዞን ግምቢቹ ወረዳ ለሚሰራው ይሄው የመታሰቢያ ሀውልት እና ፓርክ በ4 ሄክታር መሬት ላይ ሊገነባ የታሰበ ሲሆን ቦታው የማስታወሻ፣ የአረንጓዴ ቦታና የውጪ መሰብሰቢያ […]
↧