የዚህ ጽፉፍ መቸት ከጥቂት ወራት በፊት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አሁን ሥራ ላይ ያዋለውን መመሪያ ባወጣበት ወቅት ጋዜጣ ላይ የጻፍኩት ጽፉፍ ነው እነሆ፡- መሰንበቻውን የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስቴር የእምነት ተቋማትን ለመመዝገብ (ለመቆጣጠር) አንድ መመሪያ ማውጣቱና እያነጋገረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ መመሪያ የተረቀቀውና ተግባራዊ ሊደረግ ታስቦ የነበረው በተመሳሳይ ዓላማና አንቀጾች በተለያዩ ሰብአዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሰማርተው ይሠሩ የነበሩትን መንግሥታዊ [...]
↧