የዜጎችን ፊርማዎች ማሰባሰብ የብዙ መቶ አመቶች ታሪክ ያለው ሰላማዊ ትግል ነው። የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ አንዱ ግብ በኢትዮጵያ ሽብር ህግ ላይ ዜጎች ያላቸውን አቅዋም በፊርማቸው እንዲገልጹ ማድረግ ነው። እንደሚታወቀው አንድ መንግስት ዜጎቹን በሽብር ህግ የሚገዛው ከፖለቲካ ተፎካካሪዎቹ የተሻለ አሳብ በማቅረብ የህዝብ ድጋፍ ማግኘት ሲያቅተው ነው። የአዲስ አሳብ ምንጮቹ ሲደርቁበት ነው። የአሳብ ኪሳራ ሲደርስበት ፊቱን ወደ ሽብር ያዞራል። [...]
↧