የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ-ሌላ-እንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን [...]
↧