ሰላማዊ ፓርቲ የመጀመሪያውን ጥሩ አቅጣጫ አመልካች ሰላማዊ ሰልፍ ግንቦት ፳ ፭ ቀን ፳ ፻ ፭ ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባ በማድረግ፤ የሕዝቡን የነፃነት ፍላጎት ባደባባይ አሳዬ። ይህ ታሪካዊ ነው። ተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፎች መጪ መሆናቸውንና አይቀሬነታቸውን አረጋገጠ። ካሁን በፊት ታጋዮች፤ በተደጋጋሚ፣ በየቦታው፣ ሰላማዊና የትጥቅ አመፅ በማድረግ ግባቸውን ለመምታት ጥረት አድርገዋል። በሕዝቡ ላይ በደል እስካለ ድረስ፤ አመፅ በተለያዬ [...]
↧