ስለ ኢትዮጵያውያን ብዙ የሚያውቁ ፈረንጆች ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ጠንቀቆ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ እና ከባድ እንደሆነ ይናገራሉ። “ስለ ሕዝቡ ለመጻፍ የሚፈልግ አንድ ሰው ኢትዮጵያ በገባ ማዕግስት አንድ መጽሃፍ ሊጽፍ ይችላል፤ ይህ ሰው ሳምንት ሲቆይ አንድ መጣጥፍ ይጽፋል፣ ወር ሲቆይ ግን የሚጽፈው ይጠፋበታል።” ይላሉ። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ይመስለኛል። ኢትዮጵያ የብዙ ባህል፣ የብዙ ቋንቋና የበርካታ እምነት ሃገር ስብስብ [...]
↧