ዕለተ ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. በቃሊቲ አውቶቡስ መናኸሪያ የተገኘነው ማልደን ነበር። መናኸሪያው እንደ ወትሮው ግርግር አይታይበትም። አለፍ አለፍ እያሉ ወደ መናኸሪያው የሚገቡ ሰዎችም በቀጭን ገመድ ራሳቸውን ከልለው የኮሮና ሙቀት በሚለኩ ሰዎች እየተፈተሹ ይገባሉ። ምንም ዓይነት የቅድመ ጥንቃቄ የምክር አገልግሎት ሲሰጥ ግን አላየንም። አውቶቡሱ ከመነሳቱ በፊት ረዳቱ በር ላይ የተለካውን የሰውነት የሙቀት ልኬት የተነገረንን […]
↧