ከእስረኞች ጠበቆች ጋር የተደረገው ውይይት ታፈነ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከአሜሪካ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመሆን በኢትዮጵያ እስር ቤት ለሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ አስረኞች ጥብቅና ከቆሙ የህግ ባለሙያዎች ጋር ለመነጋገር ያደረገው ሙከራ ታፈነ። የጋራ ንቅናቄው ለጎልጉል እንዳስታወቀው ዓርብ ሰባት ከሚሆኑ ጠበቆች ጋር ለመያየትና መረጃ ለመለዋወጥ መስመር ተዘርግቶ ነበር። አቶ ኦባንግ ሜቶና የጋራ ንቅናቄው የሚዲያ ዴስክ፣ [...]
↧