በተከታታይ የጻፍካቸውን ሁለት ግሩም መጣጥፎች በፍቅር አነበብኳቸው፡፡ በነዚህ ጽሑፎች እንደተረዳሁት ጥሩ አንባቢ ነህ፤ የብዕር አጣጣልህም ውብ ነው፡፡ ሀገርህንም እንደምትወድ በጽሑፍህ ብቻ ሣይሆን በረሃ መውረድህ ራሱም በቂ ምሥክር ነው፡፡ ማቄን ጨርቄን ሳትል ለአንዲት እናትህ ኢትዮጵያ ስትል እያሳለፍከው ያለኸውን መከራና ስቃይ መረዳት እችላለሁና የእምዬ አምላክ ይከተልህ፡፡ አንተን ብቻም ሣይሆን ለተመሳሳይ በጎ ዓላማ የተሰለፋችሁትን ጓዶችህንም ሁሉ ፈጣሪ ይጠብቃችሁ፤ […]
↧