የትግራይ ሕዝብ “ነጻ አውጡኝ” ብሎ ሳይሰይማቸው፣ ሳይመርጣቸው፣ ሳይጠይቃቸው፣ ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብለው የሰየሙ ወንበዴዎችና ሽፍቶች የምኒልክ ቤተመንግሥት ከገቡ 26 ዓመታት ተቆጥረዋል። በቂም፣ በበቀል፣ በክፋትና በኢሞራላዊ ተግባራት የተሞሉ፤ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ፈጽሞ የሚያጠራጥር፤ ማንነታቸው ይህ ነው ተብሎ የማይታወቅ፤ በሐሰት ስም ከበረሃ እስከ ቤተመንግሥትና ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የታዩ፤ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ የትግራይን ሕዝብ ያስጨፈጨፉ (ሐውዜንን ይጠቅሷል)፤ […]
↧