ከተወለድኩበት እለት ጀምሮ በቅጡ የማውቀው ጎጃሜነቴን ነበር። ከዚያ ልዩ የምጠራበት ስም እንዳለኝ የሰማሁት እያደር ነው። ሌላው ቀርቶ ኢትዮጵያዊ እንደምባል እንኳን የገባኝ ትምህርትቤት ገብቼ ሶስተኛ ወይም አራተኛ ክፍል ግድም ስደርስ ሳይሆን አይቀርም። ከዚያም ሙት ወቃሽ እንዳልሆን ስማቸውን የማላነሳው ግን እጅግ የምወዳቸው ዖሮሞው የህብረት አስተማሪዬ የዛሬን አያድርገውና ኢትዮጵያ 14 ክፍለሀገሮች እንዳሏት ሲነግሩኝ ለካ ከጎጃም ሌላ ሀገር አለ […]
↧