ዓይኔን በዓይኔ ያየሁበት፣ በስተእርጅና ያገኘሁት፣ የትናንቱ ማሙዬ፣ ያሳደኩት አዝዬ የንግሊዞችንወረራ ሰምቶ፣ በቴዎድሮስ ሞት ተቆጥቶ፣ ለምን? ለምን ሞተ? ብሎ ሲያለቅስ፣ የዓይኑን ዕንባ ላደርቅ- የልቡን መሰበር ላድስ፣ ጀግኖቻችንን ቆጥሬ- ታሪካችንን ባወድስ፣ ዕንባውን ዋጥ አድርጎ- በአትኩሮት ዓይኔን እያየኝ፣ «አንተስ…?» አንተስ!- ምን ሰርተሀል? በማለት ጠየቀኝ። እድሜ ቢደራረብ ተግባር ሳይላበስ፣ እንደዚህ እንደኔ ያስጠይቃል ለካስ! (ወለላዬ)
↧