አንደኛ፣ ገና በልጅነቴ አሥር ዓመት ግድም ሲሆነኝ አንድ በድቀድቂት ከእንጦጦ ወደታች የሚወርድ ኢጣልያዊና እኔ ተጋጠምን፤ እሱ በዚያ በጥቁር ድንጋይ ኮረት በረበረበበት መንገድ ላይ ሲጓዝ ወደ እንጦጦ የሚወጣ ወታደሮችን የጫነ ከባድ መኪና ቆሞ ነበር፤ በዚያ መኪና ላይ አንድ ዝንጀሮ ነበር፤ የኔ አትኩሮት በዚህ ዝንጀሮ ላይ ነበር! እንደሚመስለኝ ዝንጀሮውን እያየሁ ስሮጥ ከድቅድቂቱ ጋር ተገናኘን፤ እኔ ከስር በተረበረበው […]
↧