ጎልጉል “የዖሮምያ ሰነድ አዲሱ ቃልኪዳን” በሚል ርእስ ባወጣው ፅሁፍ የመክለፍለፍ ፖለቲካ ጎጂ አዝማሚያ በግልፅ መጠቆሙን ሳነብ እኔም “እውነትም መክለፍለፍ” ልል አማረኝ፤ እውነትም መክለፍለፍ። መቼም በኢትዮጵያ የለውጥ ታሪክ ውስጥ ልሂቃን ፖለቲከኞችና ህዝብ ሆድና ጀርባ ከሆኑ ከ40 አመት በላይ ሆኗል። ህዝብ ለሃቀኛ ለውጥ ደሙን ያፈሳል፤ ብልጡ ልሂቅ ስልጣን ይወርሳል። ህዝብ ለጋራ አላማ ይደማል፤ ልሂቅ ለግል ጥቅሙ ይሿሿማል። […]
↧