ኣንድ ጊዜ ኣባባ ተስፋየ ከዚያ ከሚያምርባቸው የ ልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅታቸው ጠፉብኝና ኸረ የት ገቡ? ብየ ኣንዱን ጠየኩ። “ኣልሰማህም እንዴ ?” በፍጹም ምን ሆኑ? ደንገጥ ብየ እንደገና ጠየኩ። ያ ሰው እየሳቀ “ባለፈው ጊዜ ኣዲሱ ኣመት የሰላምና የእርቅ ያድርግልን ብለው በመናገራቸው የመንግስት ሰዎች ማን ሲጣላ ኣዩ? ብለው ኣባረሩዋቸው እኮ!” ሲለኝ ለደቂቃዎች እንደዚያ የሳቅኩበት ጊዜ ትዝ ኣይለኝም። [...]
↧