እናት በፍቅር፣ ጽንስ ይዛ፣ ዘጠኝ ወር አርግዛ፣ ራስዋን ምግብ አድርጋ፣ በማኅጸንዋ ሸሽጋ፣ ሽሉን ወደሰውነት አሳድጋ፣ የፈጣሪን ባሕርይ ተጋርታ፣ ሰው ሆና ሰው ፈጣሪ የሕይወት አለኝታ፣ በጻዕር አምጣ ወልዳ፣ አቅፋ በፍቅር አጥብታ፣ ተጨንቃ አሳድጋ፣ እንቅልፍ አጥታ፣ ሲስቅ ሲያስቃት፣ ሲያለቅስ ሲያስለቅሳት፣ ስትቆጣው እንዲያድግላት እንዲማርላት፣ ክቡር ሰው ሆኖ እንዲያኮራት፣ ያላትን ሁሉ ከፍላ መስዋእት፣ በጉጉት ስትጠብቅ — ጨካኞች ሬሳውን ጣሉላት፡፡ […]
↧