“አንቺ እማማ ኢትዮጵያ አንቺ እናት ዓለም” ሎሬትሽ እያቆላመጠ ይነግርሽ እንደነበር በቀለም፤ እወቂበት ከእንግዲህ አብጂለት ፍቱን መላ፣ የሚሞትልሽ እንጂ የሚገልሽ ላይበላ፤ ህዋሳትሽ ይንቀሳቀስ ሰሜን-ደቡብ ምዕራብ-ምስራቅ፣ የአለላ ተምሳሌቱ የሕዝቦችሽ ህብረት ይድመቅ፤ ብድግ በይ ተራመጂ በእንፉቅቅ መዳኽሽ ያብቃ፣ የውብ ህይወት አዲስ ምዕራፍ በግዛትሽ ይገንባ! እናት አገር ባለታሪክ ተነሽ ቤትሽን አጽጂ፣ የተዝረከረከውን በፕሮፓጋንዳ ፈንጂ፣ በተከፈተው ጉድጓድ ይግባ ጠራርገሽ አስወግጂ። […]
↧