ገና ቁጭ እንዳልኩኝ ቀጥሮኝ እንዳገኘኝ እከሌ ጨርሶ «ሰው አይደለም!» አለኝ ምነው? ምን አ’ረገህ ? «ሰው አይደለም!» ስልህ እኮ! ምን አ’ረገህ? «ሰው አይደለም!» አልኩህ። ቢራችንን አዘን በዝምታ ቆየን እንደገና ደግሞ ሳሉን እየሳለ አንገቱን ነቅንቆ «ሰው አይደለም!» አለ። ሰው ይመስላል አልኩኝ ስሜቱን ልረዳ ፊቱን መረመርኩኝ ባ’ይኑ እየገረፈኝ አይምሰልህ! አለኝ ግንባሩ ታጠፈ ጥርሶቹን ነከሰ ጠረጴዛ መታ፣ ቢራችን ፈሰሰ […]
↧