የጎጆዎቻንን ገመናስ እንሸፍንበት ገዶን አያውቅም፤ ድሮ በደህናው ጊዜ፣ ኑሮ ርካሽ በነበረበት ዘመን፣ ኑሮ ከሀገራችን እድገት ጋር እንዲህ አብሮ ሳያድግ፣ የጋገርነውን የዘንጋዳ ቅይጥ፣ ባሰጣነው ማኛ፣ እርቃናችንን በሰልባጅ እንሸፍነው ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን እንደየአቅማችን ገመናችንን እንሸፍንበት አልገደደንም፡፡ ሌላው ቀርቶ መሶባችን ባዶ ሆኖ የሚበላ ቢጠፋ፣ ጦም መዋላችንን እንሸፍንበት የከራረመ ስቴኪኒ ከጥርሳችን አይጠፋም፡፡ እንደርበው ጃኬት ባይኖረን፣ ቆዳ በሚያሻክር ብርድ ሙቀቱን [...]
↧