ሰላሙ የደፈረሰበት ህዝብ የመንፈስ ጤንነት አይሰማውም። ሰላምና ጤና የሚነጣጠሉ አይደሉምና፤ የመንፈስ ጤንነት የደፈረሰበት ህዝብ ጤናማ ነው ማለት አይቻልም። “ሰላም ሳይኖር ሰላም የሚሉ ወዮላቸው!” ከሚለው ከነብያት ቃል ጋራ ተጋጨ። ይህም ብቻ አይደለም። ሰላም የሌለን ቄሶች ሰላም እንደሌለን እያወቅን፤ የተቀጠርንለት እለታዊ ገቢያችን እንዳይቀርብን “ ሰላም ለኩልክሙ” እንላለን። በጥቅሉ ልማድ አድራሾች ሆን። የተዋህዶ እምነት ተከታዮች ነን የምንል ኢትዮጵያውያን […]
↧