በአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መሥሪያ ቤት ላይ ኅብረተሰቡ የሚያሰማው እሮሮ ኤሌክትሪኩ መጥፋቱ ብቻ አይደለም፡፡ መብራቱ ሄዶ ሲመጣ የሚያደርሰው ጥፋት የትየለሌ ነው፡፡ የኤሌክትሪኩ ኃይል መጠን ከመደበኛው ውጭ ከፍና ዝቅ ሲል የሚያደርሰው ጥፋት ቤት ይቁጠረው፡፡ ማቀዝቀዣው፣ ቴሌቪዥኑ፣ አምፖሉ፣ ልዩ ልዩ “ቻርጀሮች” የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ተቃጠሉብን የሚል የሕዝብ እሮሮ በየጊዜው ይሰማል፡፡ የሚመለከተው መሥሪያ ቤት ፈጣን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አገልግሎት […]
↧