ባለፈው ሳምንት ወደ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉን የአየር መንገዱ ምንጮች አስታወቁ። በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮቹ ጠቁመዋል። በተሳፋሪዎች ላይም ከፍተኛ መጉላላት ደርስዋል። አውሮፕላኑ ካኮበኮበ በኋላ እንዲመለስ የተደረገበት ምክንያት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ ከአለምሰት ሙጬ ጋር በአውሮፕላኑ በመሳፈሩ ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል። […]
↧