በተለያየ ጊዜ በተለያየ የክህደት አስተምህሮ በመሰናከል በመውደቅ ከዚህች ሐዋርያዊት አንዲት ቤተክርስቲያ እየተለዩ በኑፋቄያዊ አስተምህሮ ጸንተው በመቀጠል ለዚህች አንዲት ሃይማኖት አንዲት ቤተክርስቲያን ጠላቶች የሆኑ ዲያብሎስን የሚያገለግሉ ከ40 ሽህ በላይ ይቆጠራሉ፡፡ ሃይማኖት ነንም ይላሉ፡፡ ክርስቶስ በወንጌሉ ሐዋርያትም በመልእክቶቻቸው እንደተናገሩት ግን ከአንዲቷ በስተቀር ይሄ ሁሉ ሃይማኖት ነኝ ባይ ዝግንትል ሐሰተኛና ዲያብሎሳዊ የክህደትና የጥፋት መንገዶች ናቸው፡፡ የዘመኑ ፍጻሜ ሲቃረብ [...]
↧