“ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል” የሚለው ጥሬ ንባብ፤ ስለ ጅብና ስለ ቁርበት መልእክት ለማስተላለፍ አይደለም። ጅቡ የሚወክለው አካል አለ። ቁርበቱ የሚወክለው ነገር አለ። በቁርበቱና በጅቡ መካከል ያለውን ግንኙነት ሳያውቁ ቁርበቱን ለጅቡ ያነጠፉለትም የሚወክሉት አለ። ይህ አገላለጽ በኢትዮጵያዊው ቅኔ ትምህርት፣ ቀመር፣ ስልት ሲመዘን፤ ጅቡ ሰም ነው። ቆርበቱም ሰም ነው። ሁሉም ሰም ነው። ወርቁ ከሰሙ [...]
↧